Search

የጥናትና የምርምር ውጤቶች በንድፈ ሀሳብ እና በጽሑፍ ደረጃ ተወስነው መቅረት የለባቸውም -የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)

ሓሙስ ሐምሌ 16, 2018 128

በአፍሪካ ደረጃ የሚወሰኑ ዋና ዋና የፖሊሲ እና የልማት ውሳኔዎች ሀገራቱን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር በእውነተኛ፣ አሳታፊ እና ግልጽ በሆኑ መረጃዎችና የምርምር ውጤቶች ላይ የተመሰረቱ ሊሆኑ እንደሚገባ የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (/) ተናገሩ።

ሚኒስትሯ ይህንን ያሉት በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እና በአፍሪካ የተፅዕኖ ግምገማ ተመራማሪዎች መረብ አዘጋጅነት መካሄድ በጀመረው 14ኛው የአፍሪካ የፕሮግራም መረጃ እና ማስረጃ ጉባዔ ላይ ነው።

ፈጣን የቴክኖሎጂ ለውጦችን፣ የአየር ንብረት ስጋቶችን እና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት የሚያስከትሏቸውን ጫናዎች ለመወጣት የምርምር መረጃዎችን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም አመልክተዋል።

የጥናትና የምርምር ውጤቶች በቀጥታ ወደ በጀት ውሳኔዎች፣ ወደ መንግሥት ፕሮግራሞች እና ወደ ተግባራዊ የልማት ሥራዎች መተርጎም እንዳለባቸው ሚኒስትሯ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በእውነተኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ አሠራርን ለመገንባት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ማድረጓን ጠቅሰው የብሔራዊ ስታቲስቲክስ አገልግሎትን አሠራር ከእጅ ሥራ ወደ ሙሉ ዲጂታል መረጃ ሥርዓት የመቀየር ሂደት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

አፍሪካ ያላትን ወጣት ሕዝብ እና የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም 2063 አጀንዳን እና ሀገራዊ የልማት ግቦችን ለማሳካት ወቅታዊና አስተማማኝ የመረጃ ስርአት መገንባት ወሳኝ መሆኑ አስገንዝበዋል።

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፈቃዱ ፀጋ በበኩላቸው በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የፖሊሲ ውሳኔዎች፣ ሀገራዊ ልማትን እና መልካም አስተዳደርን በላቀ ሁኔታ ለማረጋገጥ በመረጃ እና በሳይንሳዊ የምርምር ውጤቶች ላይ የተመሰረቱ ሊሆኑ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የምርምር ውጤቶች በቢሮዎች እና አካዳሚክ ተቋማት ተወስነው መቅረት የለባቸውም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ተመራማሪዎች እና የፖሊሲ አውጪዎች ቅርብ ግንኙነት በመፍጠር መረጃዎችን ለተግባራዊ ውሳኔዎች ማዋል እንዳለባቸው አንስተዋል።

የውጤታማ ዓለም አቀፍ እርምጃ ማዕከል (CEGA) መሥራች ዳይርክተር ኤድዋርድ ሚጌል እንደገለፁት የአየር ንብረት ለውጥ፣ የኢኮኖሚ ተግዳሮቶችና ሌሎች የልማት ችግሮች በተጨባጭ ማስረጃ ላይ ተመስርተው ሊፈቱ ይገባል ብለዋል

የመረጃ ትንተና እና የምርምር ውጤቶች ተግባራዊ መፍትሔዎችን ለማቅረብ መሠረት መሆናቸውም አብራርተዋል።

በወንድማገኝ ሀይሉ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: