የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች በጋራ መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ ወቅት የኢንስቲትዩቱ መሥራች፣ ሊቀመንበር እና የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ቶኒ ብሌየር፤ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን እያዘመነ ስለመሆኑ በመናገር ተቋማቸው ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ሙሉ ቁርጠኝነት ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው የቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ለመደገፍ እያደረገ ላለው አበርክቶ ምስጋና አቅርበዋል።
ሁለቱ ተቋማት በኢትዮጵያ ያለውን የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ልማት እና ተግባራዊነት ለማረጋገጥ ቀጣይነት ባለው መልኩ በጋራ እንደሚሰሩም ተመላክቷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: