Search

በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት በሁሉም ወረዳዎች የመሶብ አገልግሎት ተደራሽ ይደረጋል - የፌዴራል መሶብ አገልግሎት

ዓርብ ሐምሌ 17, 2018 195

የመሶብ አገልግሎት ዘላቂና ተደራሽ ለማድረግ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የመሶብ አገልግሎት የሚመራበት ስትራቴጅክ ዕቅድ በፌዴራል መሶብ አገልግሎት ተዘጋጅቷል።

‎የፌደራል፣ የከተማ አስተዳደሮች እና የክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሥራ ኃላፊዎች በስትራቴጂክ ዕቅዱ ላይ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

‎በ2017 ዓ.ም ተግባራዊ የተደረገውና መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ከብልሹ አሠራር የፀዳ ለማድረግ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ‎በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተጀምሮ፣ አሁን ላይ በሁሉም ክልሎች 100 የመሶብ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ወደ ሥራ መግባታቸው ተገልጿል።

‎በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ ሦሶት ተንቀሳቃሽ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰጪዎች እና ዜጎች ባሉበት ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበት የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ በዚህ ዓመት ወደ ሥራ መግባቱ ተመላክቷል።

‎በፌዴራል መሶብ አገልግሎት የተዘጋጀው ስትራቴጂው፣ ከ2019 እስከ 2021 ዓ.ም የሚተገበር ሲሆን፣ መሶብ አገልግሎት ተቋማዊ አሠራሩን ለማዘመን፣ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልና ተደራሽነቱን ለማስፋት የሚያስችሉ ትልሞችን ይዟል።

‎በስትራቴጅው መሠረት በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት በሁሉም ወረዳዎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽ እንደሚደረግና ‎ተንቀሳቃሽ እና ራስ አገዝ የመሶብ አገልግሎትን ለማስፋት እንደሚሠራ ተገልጿል።

‎በባዬ ሙላት

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: