የማዕከላዊ ኢንዶኔዢያ ሱላዊሲ ግዛት በሬክተር ስኬል 6 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በመከሰቱ በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን የሀገሪቱ የአደጋ መከላከል ኤጀንሲ አስታወቀ።
በአደጋው እስከ አሁን 29 ሰዎች መጎዳታቸውን እና 2 ሰዎችም በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ኤጀንሲው ገልጿል።
ከባድ የመሬት መንቀጥቀጡ ከተከሰተ በኋላ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ሰዎችን ከፍርስራሾች ውስጥ እንዲወጡ እያደረጉ መሆኑ ታውቋል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት በተለያዩ የኢንዶኔዥያ አካባቢዋ ላይ መሰማቱንም ሬውተርስ ዘግቧል።
በሴራን ታደሰ
አዳዲስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የኢቢሲን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር እና ፕለይ ስቶር አውርደው ዲጂታል ኢቢሲን ይቀላቀሉ።
አንድሮይድ (Android) ስልክ የምትጠቀሙ በዚህ ሊንክ ➡️ https://shorturl.at/6KegY
አይኦኤስ (iOS) ስልክ የምትጠቀሙ ደግሞ በዚህ ሊንክ ➡️ https://shorturl.at/hFuA1