ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት የኀዘን መግለጫ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የኪነ ጥበብ ታሪክ ታላቅ ዐሻራ ያሳረፈው አርቲስት ደበበ እሸቱ በማረፉ ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።
ደበበ እሸቱ ለዘመናዊት ኢትዮጵያ ቴአትርና ፊልም ዕድገት ፋና ወጊ ከሆኑት ልሂቃን አንዱ ነው ሲሉም አስፍረዋል።
ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ በጽናት እንድታሳካ በኪነ ጥበብ ተሰጥዖው ያበረከተውን ሚና ዘወትር ስናስታውሰው እንኖራለን ብለዋል።
ፈጣሪ ነፍሱን ያሳርፍ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃዘናቸውን ገልጸዋል።