Search

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በአርቲስት ደበበ እሸቱ ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

እሑድ ነሐሴ 11, 2017 114

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በአርቲስት ደበበ እሸቱ ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጸዋል።
አርቲስት ደበበ እሸቱ ለውድ ሀገሩ ኢትዮጵያና ለሕዝቧ በነበረው ጥልቅ ፍቅር፣ ለኪነጥበብ ዕድገትና ለእውቀት መዳበር ባበረከተው አስተዋጽኦ ሲታወስ ይኖራልም ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
ፕሬዚዳንት ታየ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት የሀዘን መልዕክት አንጋፉውና ተወዳጁ የኪነጥበብ ሰው ደበበ እሸቱ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየቱ የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እገልጻለሁ ብለዋል።
ደበበ ለውድ ሀገሩ ኢትዮጵያና ለሕዝቧ በነበረው ጥልቅ ፍቅር፣ ለኪነጥበብ ዕድገትና ለእውቀት መዳበር ባበረከተው አስተዋጽኦ ሲታወስ ይኖራል ሲሉም ነው የገለጹት።
 
ሕይወቱን ለእውነትና ለጥበብ የሰጠ፣ ለትውልድ አርአያ የሆነ ታላቅ ሰው ነበር ያሉት ፕሬዚዳንት ታዬ ነፍስህ በሰላም ትረፍ ሲሉም ገልጸዋል።