Search

አርቲስት ደበበ እሸቱ በሥራው ሁሉ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን እንደወገነ የኖረ ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

እሑድ ነሐሴ 11, 2017 157

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአርቲስት ደበበ እሸቱ ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “በሥራው ሁሉ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን እንደወገነ በኖረው የሀገራችን የኪነጥበብ አድባር ደበበ እሸቱ ህልፈት የተሰማኝ ሃዘን ጥልቅ ነው” ብለዋል።
የእርሱ ውግንና ሁሌም ለኢትዮጵያ ሆኖ ለመዝለቁ በዘመኑ ሁሉ የሰራቸው የጥበብ አሻራዎቹ የተግባሩ ህያው ምስክሮች እንደሆኑም ነው ያነሱት።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደበበ ከወጣትነት እስከ ሕልፈቱ ለኢትዮጵያና ለኪነጥበብ የተጋ፣ ከሥራው ሞት የለየው ብርቱ ሰው ነው፤ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለአድናቂዎቹ እና ለኪነጥበብ ማኅበረሰብ መጽናናትን እመኛለሁም ብለዋል በመልዕክታቸው።