በነፃነት የሚውለበለበው ነጭ የሰላም ዓርማ የፍርሃትን ድምፅ በመግባባት የመተካት፣ የመለያየትንም ጥላ በአንድነት ብርሃን የማሸነፍ ታላቅ የተስፋ ምልክት ነው።
በኢትዮጵያ የተጀመረው ሀገራዊ ምክክርም ይህንኑ የሰላም መልዕክት በልቡ ሰንቆ የተነሳ ጥረት ነው።
የተለያዩ ሀሳቦች፣ ታሪኮች እና ልምዶች ወደ አንድ የውይይት ጠረጴዛ መጥተው በመነጋገር፣ የጋራና ብሩህ መጪውን ጊዜ ለመገንባት የሚያስችል አዲስ መንገድ ተከፍቷል።
ነጭ የሰላም ዓርማ በነፋስ ሲውለበለብ እንደሚያሳየው፣ ሰላም በዝምታ ወይም በግዴለሽነት የሚመጣ ሳይሆን በሰፊው በመስማማት፣ በመረዳዳት እና በግልጽ በመነጋገር የሚገነባ ህያው እሴት ነው።
ሀገራዊ ምክክርም የተለያዩ ድምፆችን ለማጥፋት ሳይሆን፣ ሁሉም ድምፆች እኩል እንዲደመጡና ለተወሳሰቡ ሀገራዊ ፈተናዎች የጋራ መፍትሔ እንዲፈለግላቸው የሚያስችል የሰላም መንገድ ነው።
ይህ በክብር የሚውለበለበው ነጭ ዓርማ ለኢትዮያውያን ትልቅ ጥሪ ያስተላልፋል፤ ይህም ያለፈውን ታሪክ በጥበብ በመማር፣ ልዩነቶቻችንን በማክበርና በመቀበል፣ በጠንካራ ምክክር የተገነባች ጸንታ የምትቆም የጋራ ሀገር ማቆም እንደሚቻል ማረጋገጫ ነው።
ምክክር የሰላም ድልድይ ከሆነ፣ ነጩ የሰላም ዓርማ ደግሞ ወደዚያ ድልድይ የሚጠራ የተስፋ መብራት ነው። ኢትዮጵያ የነገዋን ገጽታ በግጭት ሳይሆን በመደማመጥ፣ በመተማመን እና በዘላቂ ሰላም እንድትፅፍ የሚያበረታታ ታላቅ የጋራ ምልክታችን ሆኗል።
በልዩ እሸቱ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: