Search

የወሎ ተርሸሪ ኬርና የሕክምና ማስተማሪያ ሆስፒታል - በነገው አዲስ ቀን የዜና መሰናዶ የሀገር ጉዳይ

እሑድ ነሐሴ 11, 2017 116

ነገ በአዲስ ቀን የዜና መሰናዶ የሕዝብ ጥያቄዎች በስፋት ሲያስተናግድ የቆየው የወሎ ተርሸሪ ኬርና የሕክምና ማስተማሪያ ሆስፒታል ጉዳይን እናነሳለን።

በኢትዮጵያ ብሎም በምስራቅ አፍሪካ  ያለውን የሕክምና ዘርፍ ለማዘመንና ያለውን የሕክምና ችግር ለመፍታት ተስፉ ተሰንቆበት የነበረው የሆስፒታሉ ግንባታ መጓተትና ከሕዝብ የተሰበሰበው ገንዘብ ከዓላማ ውጭ ማዋሉ ሲገለፅ ቆይቷል።

የሆስፒታሉ ግንባታ ከመንግስት ባሻገር በሕዝብ ድጋፍ የተጀመረና የማኅበረሰቡን የሕክምና ጥያቄ ይመልሳል ተብሎ የሚጠበቅ ነበር።

ኢቢሲም በይዘት ማሻሻያው ከ8 ወር በፊት የጀመረው አዲስ ቀን የዜና መሰናዶ፥ የመጀመሪያ የሀገር ጉዳይ አድርጎ ይህንኑ የሕዝብ ጥያቄ በስፋት አንስቶ እንደነበር ይታወሳል። በተደጋጋሚ አጀንዳ በማድረግ ሲሰራም ቆይቷል።

ታዲይ አሁን ላይ ይህ ታላቅ ፕሮጀክት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተቀመጠለት የጊዜ ገደብና በተላለፈ ውሳኔ፤ ፕሮጀክቱን የወሎ ዩኒቨርስቲ እንዲያስተዳድር በይፉ ተረክቧል።

 ኢቲቪ በነገው በአዲስ ቀን የዜና መሰናዶ የሀገር ጉዳይ የዚህን የርክክብ ሥነ-ሥርዓት፣ የሕዝቡን ስሜትና በቀጣይ በሚሰሩ ጉዳዮችን በስፋት ይዳስሳል።

አዲስ ቀን የዜና መሰናዶ ይህንን የሀገር ጉዳይ ጨምሮ ሌሎች ጥንቅሮችን ይዞ ነገ ጧት ከ1:00 እስከ 3:00  ከሰናይት ብርሀኔና ከሀብታሙ ተክለ ሥላሴ ጋር ይጠብቃችኋል።

አዲስ ቀን!