ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዘርባጃን ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሳሂባ ጋፋሮቫ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማካሄዳቸውን አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከአፈ ጉባኤዋ ጋር ያደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን እና የአዘርባጃንን ስትራቴጂያዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት የጋራ ዕድገት በሚያሳድጉ የትብብር መስኮች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውጤታማ ሐሳብ መለዋወጣቸውንም ገልጸዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: