Search

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በማዕድን ዘርፍ ላይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው እድሎች እና የትብብር መስኮች ዙሪያ ተወያዩ

ረቡዕ ሐምሌ 22, 2018 35

የማዕድን ሚኒስትሩ / ሀብታሙ ተገኘ በአሜሪካ መንግሥት የመካከለኛው ምሥራቅ እና አፍሪካ ምክትል ረዳት ሚኒስትር ማርክ ሚሼል የተመራ ከፍተኛ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም አሜሪካ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው እድሎች እና የትብብር መስኮች ዙሪያ በሰፊው መክረዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን የገለጹት ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኘ የአሜሪካ ኩባንያዎች በሀገሪቱ በማዕድን ልማት እና ኢንቨስትመንት ተሰማርተው መስራት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ምክትል ረዳት ሚኒስትሩ ማርክ ሚቼል በበኩላቸው በኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ እየተከናወነ ያለውን ለውጥ ያደነቁ ሲሆን፣ የአሜሪካ ኩባንያዎች በዘርፉ አብረው ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት እና ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: