Search

በሀዋሳ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

ሓሙስ ሐምሌ 23, 2018 86

 

ትናንት ማምሻውን በሀዋሳ ከተማ በበረዶ እና ኃይለኛ ንፋስ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች ንፋሱ ዛፎችን እና የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በመጣሉ የ1 ሰው ሕይወት ሲያልፍ፣ በ10 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱ ተረጋግጧል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በመሠረተ ልማት ላይ በተከሰተው ውድመት ምክንያት በከተማዋ በስፋት የመብራት አገልግሎት ምሽቱን ተቋርጦ አድሯል።

 

 

በቀጣዮቹ ቀናትም ኃይለኛ ንፋስ የታጀበ ዝናብ እና የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል የጠቆመው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

በፈቃደ አብ አለማየሁ

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: