መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ዑለማዎች፣ ምሁራኖች፤ ወጣቶች፣ ሴቶችና የሥራ ማህበረሰብ የ2017 የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች የአመራር ምርጫ በመላ ሀገሪቱ የመጀመሪያ ደረጃ የመስጂድ ምርጫ ሲካሄድ ቆይቶ በስላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የ2017 ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ጽ/ቤት ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ሁሉም ክልሎች ምርጫውን ከነሐሴ 9/ 2017 በዑለማዎች ጀምሮ ዛሬ ነሐሴ 11/ 2017 በአራቱ ዘርፎች ማለትም በምሁራን፣ ወጣቶች፣ ሴቶችና የሥራ ማህበራት እስከ ቀነ- 12 ሰዓት ድረስ በመምረጥ መጠናቀቁም ተገልጿል።
ምርጫውን በማስተባበር፣ በመምራት እንዲሁም አጠቃላይ ይዘቱ መስመሩን ይዞ እንዲሄድ ላደረጋችሁት ተሳትፎ፣ ከመንግሥት ለተደረገው የፀጥታ ድጋፍ ምስጋናችን የላቀ ነው ብሏል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የ2017 ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ጽ/ቤት።
የቀሩትን ከወረዳ እስከ ፌደራል የምክር ቤት ምስረታዎች በጉልህ፣ በሙሉ ሞራል፣ ተሳትፎ እና ተነሳሽነት ይካሄድ ዘንድም ም/ቤቱ መልዕክት አስተላልፏል።