ከመስከረም 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኛው ተጨማሪ የደመወዝ ማሻሻያ ለማድረግ መንግሥት ወስኗል፡፡ በዚሁ ማሻሻያ መሠረት፦
1. ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 4,760 ወደ ብር 6,ዐዐዐ እንዲያድግ
ይደረጋል፡፡
2. የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6,940 ወደ ብር 11,500 ይሻሻላል።
3. ከሲቪል ሰርቪስ ውጭ በተለያዩ ዘርፎች የተሠማሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝም
ማሻሻያ ይደረግበታል፡፡
4. ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ከብር 21,492 ወደ ብር 39,000
እንዲያድግ ይደረጋል፡፡