በናይጄሪያ ሶኮቶ ግዛት፣ ከ50 በላይ ሰዎችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ባጋጠማት የመስመጥ አደጋ የ10 ሰዎች ሕይወት ማልፉ ተዘገበ።
በደረሰው የጀልባ መስመጥ አደጋ ከ40 በላይ ሰዎችን እስካሁን ማግኘት እንዳልተቻለም ነው የተገለፀው።
የነፍስ አድን ሠራተኞች የጠፉ ሰዎችን ፍለጋ ላይ መሆናቸውን የሀገሪቱ የድንገተኛ አደጋ ተቋም አስታውቋል።
በተመሳሳይ ከሁለት ቀናት በፊት በማዕከላዊ ኒጀር ግዛት በሌላ የጀልባ አደጋ ቢያንስ 13 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።
በናይጄሪያ ከጥገና ጉድለት እና በዝናብ ወቅት በሚከሰት ጎርፍ ምክንያት የጀልባ አደጋዎች በተደጋጋሚ ይከሰታሉ ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል።
በሴራን ታደሰ