የአርቲስት ደበበ እሸቱ ሥርዓተ ቀብር ነገ ነሀሴ 13 ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በ4 ኪሎ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል።
በነገው ዕለትም ከረፋዱ 5 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቴአትር ቤተሰቦቹ፤ ወዳጅ ዘመዶቹ እና የሙያ አጋሮቹ በተገኙበት የአስክሬን ሽኝት የሚደረግለት ይሆናል።
የአርቲስት ደበበ እሸቱ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴዔታ ነብዩ ባዬ እና የሙያ አጋሮቹ በመግለጫው ወቅት በአርቲስት ደበበ እሸቱን ሕልፈት የተሰማቸዉን ሀዘን ገልጸዋል።
በቢታኒያ ሲሳይ