Search

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቋል

እሑድ ሐምሌ 26, 2018 69

ከክልሉ የግብርና ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው "ተስፋን እንትከል!" በሚል መሪ ቃል ነገ የሚከናወነው የችግኝ ተከላ በክልሉ ሁሉም ዞኖች ይካሄዳል።

ጥምር ግብርናን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች የሚተከሉበት ቦታዎች ቅድመ ልየታም ተጠናቅቋል።

ባለፉት 7 ዓመታት በክልሉ የተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በደን መመናመን ምክንያት የተጎዱ መሬቶች እንዲያገግሙ በማድረግ ክልላዊ የደን ሽፋኑ እንዲሻሻል አስተዋጽኦን አበርክቷል።

የአፈር መሸርሸርን በመከላከል የክልሉ ምርታማነት እንዲጨምር ከማስቻሉም ጎን ለጎን የክልሉ ነዋሪዎች ለምግብነት እና ለኢኮኖሚ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ተክሎችን የማልማት ባህል አጠናክረው እንዲቀጥሉ መነሳሳትን ፈጥሮላቸዋል።

ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በማሳተፍ ተጨባጭ ውጤቶችን አስመዝግባለች።

በአንድ ጀምበር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን የመትከል የዓለም ክብረ ወሰንን ጨምሮ ባለፉት ሰባት ዓመታት 48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የመትከል ተግባር አከናውናለች።

በሰለሞን ባረና

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: