Search

“ኢትዮጵያውያን ዛሬ በአንድነት በመትመም አዲስ ተዓምር ሠርተዋል” - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ሰኞ ሐምሌ 27, 2018 32

ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመትመም ዛሬም አዲስ የአረንጓዴ ልማት ተአምር መስራታቸውንና በአንድ ጀምበር 805.3 ሚልዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ተአምር መፈጸሙን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አለን መልእክት፣ ባለፉት የአረንጓዴ ዐሻራ ዓመታት ዛሬን በማሰብ ምግብ መመረቱን እና ለነገ ኃላፊነት ደግሞ ደን መለማቱን ገልጸዋል።

እንደ ሕዝብ የተጋነው ፍሬ አፍርቷል፤ ተራሮች አረንጓዴ ካባ ደርበዋል፣ ዉኆች እንደገና መንጭተዋልያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የተራቆተው ለብሶ፣ የጠፋው ተመልሶ፣ የደፈረሰው ጠርቶ እንዲሁም የነጠፈው አፍርቶ የሀገር መልክ መቀየሩን እና ይሄንን ያየው ዓለምም ለትጋታችን ደጋግሞ ዕውቅና መስጠቱን አብራርተዋል።

በራዕይ ማቀድን፣ በትጋት ወዳሰቡት መራመድን፣ ጽፈው ብቻ ሳይሆን ከተናገሩት በላይ ኖረው፣ ቃላቸውን በአርአያነት ተግብረው ላሳዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) በአረንጓዴ ዐሻራ ለመጣው ስኬት ምስጋና እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

መሪ እና ሕዝብ ለአንድ ዓላማ በመሰለፍ አፈር ነክተው፣ ጭቃ ረግጠው ተስፋን መትከላቸውን የጠቀሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤እነርሱ ዝቅ ብለው ሀገርን ከፍ አደረጉብለዋል። ኢትዮጵያውያንም የመሪያቸውን ጥሪ ተቀብለው፣ ከሠርቅ እስከ ሰርክ ተምመው፣ የአየር ሁኔታውን አሸንፈው ዕቅዳቸውን ማሳካታቸውን ገልጸዋል።

ዛፍ የሚተከለው ለትውልድ በመሆኑ ከጥላው ያረፉ፣ ከድርቅ የተረፉ፣ ከፍሬው የቀመሱና ከልምላሜው የተቋደሱ ሁሉ የሚያመሰግኑ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የዘንድሮውን የአንድ ጀንበር ሕልም መሳካቱን እና ለቀሪውም በርተው በሁለመናዋ የበለጸገች አረንጓዴ ኢትዮጵያን የመገንባት ስራ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: