በከተማ አስተዳደሩ የምግብ ዋስትናን የሚያጠናክሩ፣ የደን ሽፋንን የሚያሳድጉና የከተማዋ ውበትን የሚጨምሩ ችግኞች ይተከላሉ ።
ጎርፍን ጨምሮ በተለያዩ የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ የሆነችው ድሬዳዋ ይህንን ተጋላጭነቷን ለመከላከል የአንጓዴ አሻራን ተግባራዊ በማድረግ ውጤት እያመጣች ነው።
በነገው ዕለትም ከሚተከለው ችግኝ ውስጥ 60 በመቶ ለምግብነት 40 በመቶ ደግሞ የደን የሚሆኑ ናቸው።
ለመርሀ ግብሩ ችግኞችን የማሰራጨትና ጉድጓዶችን ከማዘጋጀት ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል።
የከተማ ነዋሪዎችና አመራሮችም ለነገው መርሀ ግብር አሻራቸውን ለማሳረፍ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ለነገው መርሀ ግብርም ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ከዚህ ቀደም የተተከሉ ችግኞች ፍሬ እየሰጡ መሆናቸውና በከተማዋ ስነ ምህዳር ላይ አወንታዊ ለውጥ እያመጡ ስለመሆናቸውም ገልፀዋል ።
በአባዲ ወይናይ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: