Search

በአማራ ክልል የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ቅድመ ዝግጅት ተጠናቀቀ

እሑድ ሐምሌ 26, 2018 63

ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር ለአንድ ዓላማ የሚሰለፉበት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሀሳብ ይካሄዳል።

ለዚህም በአማራ ክልል የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።

በክልሉ በወል፣ በተቋማት እና በግለሰቦች ይዞታ ስር በሚገኙ 261 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ የጉድጓድ ዝግጅት ተጠናቅቋል።

ለምግብነት የሚውሉ ለጥምር ደን ልማት እና ለአፈር ለምነት ማሻሻያ የሚረዱ የአትክልት፣ የፍራፍሬ እና የደን ችግኞች ዝግጅት ሲከናወን የቆየ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ወደ ተከላ ቦታዎች የማጓጓዝ ሥራ መጠናቀቁን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።

በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ለፍራፍሬ ችግኞች ልዩ ትኩረት የተሰጠ ሲሆን፤ በበጋ መስኖ ጭምር በመደገፍ በሰፋፊ ክላስተሮች የሙዝ፣ የፓፓያ፣ የአቮካዶ እና የቡና ችግኞችን ማዘጋጀት ተችሏል።

በአማራ ክልል ባለፉት የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ ትግበራ ዓመታት 10 ነጥብ 6 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፤ የጽድቀት መጠናቸውም 81 በመቶ መድረሱ ተመላክቷል።

ራሔል ፍሬው

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: