Search

በአማራ ክልል "ትምህርት ለትውልድ " በሚል መሪ ሃሳብ የ2018 የትምህርት ዘመን የአንድ ቀን ጀምበር የተማሪዎች ምዝገባ ተጀምሯል

ሰኞ ነሐሴ 12, 2017 215

2018 የትምህርት ዘመን የአንድ ቀን ጀምበር ምዝገባ በአማራ ክልል ሲጀመር በምስራቅ ጎጃም የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ዛሬ ተጀምሯል። 

የምስራቅ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች በመጭው የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው በሚመለሱበት ላይ ውይይት አካሄደዋል። 

በውይይቱ ላይያለፈው የህጻናት ትምህርት ብክነት የማይጸጸት አካል ባለመኖሩ አሁን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ድርሻችንን ልንወጣ ይገባልብለዋል ወላጆች።

በምስራቅ ጎጃም ዞን በስናን ወረዳ በረዕቡ ገበያ የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት፣ በአነደድ ወረዳ በሁለት ትምህርት ቤቶች  እንዲሁም በአማኑኤል ከተማ አስተዳድር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች 2018 የትምህርት ዘመን የአንድ ቀን ጀምበር የተማሪ ምዝገባ እየተካሄደ ነው። 

በምስራቅ ጎጃም ዞን በገጠር ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ ነዋሪዎች 2018 የትምህርት ዘመን ህፃናት ልጆቻችን ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ አለባቸው ብለዋል።