Search

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ፣ የወጣቶች ሚና እና የኢትዮጵያ መጻኢ ዕድገት

ሓሙስ ሐምሌ 30, 2018 34

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ለኢትዮጵያ ወጣቶች ያስተላለፉት የክረምት ወቅት የሥልጠና ጥሪ ሀገራችን ወደ ዕውቀት-መር የዲጂታል ዘመን እያደረገች ያለውን ጉዞ በግልጽ የሚያሳይ ነው።

5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭን መሠረት ያደረገው ይህ መልዕክት ወጣቶች የዕረፍት ጊዜያቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ ወደሚያደርጋቸው የቴክኖሎጂ ክህሎት እንዲቀይሩት የሚያስችል ግዙፍ ሀገራዊ ራዕይ ሰንቋል።

'ዩዳሲቲ' በኩል በነጻ የሚሰጡት እና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው የመሠረታዊ ኮዲንግ፣ የዳታ ሳይንስ፣ የመተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ልማት እና የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ሥልጠናዎች ወጣቶች የነገዋን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ የመገንባት አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ የተመቻቹ ወሳኝ ዕድሎች ናቸው።

በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በአራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት እና በፈጣን የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዕድገት ውስጥ በሚገኝበት ነባራዊ ሁኔታ፣ የዲጂታል ክህሎት ባለቤት መሆን የሕልውና እና የብቃት ማረጋገጫ ሆኗል።

ኢትዮጵያም ይህንን ዓለም አቀፍ ተፎካካሪነት በመገንዘብ 'ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025' በስኬት በማጠናቀቅ፣ 'ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030' ስትራቴጂን ወደ መተግበር ተሸጋግራለች።

የቴሌኮም ዘርፉን ክፍት በማድረግ የኢንተርኔት ተደራሽነትን ማሳደጓ፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን 48 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ዘንድ ማድረሷ፣ እንዲሁም የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶችን በማስፋፋት የነዳጅ ግብይትን ጨምሮ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በዲጂታል መንገድ እንዲዘዋወር ማድረጓ ለዚህ የክህሎት ግንባታ ዋና አስቻይ መሠረተ ልማት ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪም እነዚህን የተዘረጉ መሠረተ ልማቶች ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ እሴት ሊለውጥ የሚችል ብቁ የሰው ኃይል የሚያፈራ በመሆኑ ከሀገራዊው የዲጂታላይዜሽን ግስጋሴ ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው።

እስካሁንም 5 ሚሊዮን በላይ ወጣቶች ሥልጠናቸውን ማጠናቀቃቸው ፕሮግራሙ ያገኘውን ሰፊ ሀገራዊ ተቀባይነት በጉልህ የሚያረጋግጥ ነው።

ጥሪው ወጣቶችን ማዕከል ማድረጉ፣ የኢትዮጵያን የሥነ-ሕዝብ ዕድል በአግባቡ ለመጠቀም የተቀየሰ ስትራቴጂያዊ እርምጃ መሆኑን ያሳያል።

60 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝቧ ዕድሜው 25 ዓመት በታች በሆነባት ኢትዮጵያ፣ ወጣቱን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ብቻ ሳይሆን ፈጣሪ እና አልሚ ማድረግ የሀገራችንን መጻኢ ብልጽግና ይወስናል።

በነጻ የሚሰጡት ዓለም አቀፍ የምሥክር ወረቀቶች፤ ወጣቶች ያለ ክፍያ እና ያለ ቦታ ገደብ ባሉበት ሆነው በዓለም አቀፉ የጊግ ኢኮኖሚ (Gig economy) ውስጥ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ሰፊ ዕድል ይከፍታሉ።

በተጨማሪም ወጣቶች ሀገር በቀል ችግሮችን የሚፈቱ አዳዲስ የፊንቴክ፣ የአግሪቴክ እና የኤሌክትሮኒክስ ንግድ መተግበሪያዎችን በመገንባት የራሳቸውን የቴክኖሎጂ ቢዝነሶች (ስታርት-አፖች) እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል።

ይህ ሂደት ወጣቶችን ከሥራ ጠባቂነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት በማሸጋገር፣ የሀገራችንን የማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት የሚያግዝ እና የወጣቶችን ተስፋ በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ጥሪ የወቅቱን የዓለም አቀፍ ቴክኖሎጂ ፍጥነት እና የኢትዮጵያን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ በሚገባ ያገናዘበ ብስል የፖሊሲ አመራር ማሳያ ነው።

ወጣቶች የክረምቱን ጊዜ በከንቱ ከማባከን ይልቅ የነገውን የቴክኖሎጂ ዓለም ለመምራት የሚያስችል ክህሎት መጨበጣቸው፣ የየራሳቸውን ሕይወት ከመቀየሩም በላይ ሀገራዊ ብልጽግናን ያፋጥናል።

5 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ተቀላቅለውት የሚገኘው ይህ ታላቅ የዲጂታል ንቅናቄ የነገዋን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ የበለጸገች እና በዓለም አቀፍ መድረክ ተፎካካሪ እንድትሆን የሚያስችላት መጻኢ ተስፋዋ ብሩህ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

በለሚ ታደሰ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: