Search

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ትግበራ ባመጣችው ለውጥ፣ ፓኪስታን በዓለም መድረክ ስትራቴጂያዊ አጋሯ አድርጋ ትሰራለች፡- የሀገሪቱ ሴኔት መሪ ዩሱፍ ራዛ ጌላኒ

Aug 18, 2025

ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ትግበራ ባመጣችው ለውጥ ፓኪስታን በዓለም መድረክ ስትራቴጂያዊ አጋሯ አድርጋ እንደምትሠራ የሀገሪቱ ሴኔት መሪ እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዩሱፍ ራዛ ጌላኒ ገለጹ።
በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባሰናዳው መድረክ የፓኪስታን ሴኔት መሪ ዩሱፍ ራዛ ጌላኒ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ እየተሰራ ያለው ሥራ የአየር ንብረት ለውጥ ችግርን በተፈጥሯዊ መንገድ መፍትሄ ያበጀ በመሆኑ ፓኪስታን በጋራ የትብብር ከፍታዋ አድርጋ ከኢትዮጵያ ጋር ትሠራለች።
በፓኪስታን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በሀገር ውስጥ የተገኘውን የዘርፉን ውጤት ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ትግበራ እየተጠቀመችበት ስለመሆኑም አንስተዋል።
ኢትዮጵያና ፓኪስታን የጀመሩትን የዲፕሎማሲ ግንኙነት በዓለም መድረክ የአየር ንብረት ለውጥ ፍትህ እንዲሰፍን ዓይነተኛ መታገያ ለማድረግ እየሰሩ ስለመሆኑም አክለው ተናግረዋል፡፡
ባለፋት ሦስት ቀናት ከተለያዩ ክልላዊ መሥተዳደሮች የተውጣጣ የወጣቶች ልዑክ በፓኪስታን ከተሞች የኢትዮጵያን ተሞክሮ የማጋራትና የአረንጓዴ አሻራ ተከላ መርሐ ግብር በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በሰዒድ ዓለሙ