Search

ፍልስጤም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በወይዘሪት ዩኒቨርስ የቁንጅና ወድድር ልትሳተፍ ነው

Aug 18, 2025

ፍልስጤማዊቷ የቁንጅና ንግሥት ናዲን አዩብ ሀገሯ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ በምትሆንበት የወይዘሪት ዩኒቭርስ (Miss Univers) የቁንጅና ውድድር እንደምትሳተፍ ተሰምቷል።
የ27 ዓመቷ ወጣት ናዲን አዩብ ሀገሯን ወክላ ታይላንድ በሚደረገው የዓለም ወይዛዝርት ውድድር ላይ ተሳታፊ እንደምትሆን የፍልስጤም ባለሥልጣናት ናቸው የተናገሩት።
ሥነ-ጽሑፍ እና ሥነ-ልቦናን ያጠናችው ናዲን አዩብ በ2022 የወይዘሪት ፍልስጤምን የቁንጅና ዘውድ መድፋቷ ይታወቃል።
በፍልስጤማዊያን ዘንድ ተስፋ የተጣለባት ናዲን በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር የፊታችን ኅዳር ወር 2025 በታይላንድ ከዓለም ዙሪያ ከተወጣጡ ቆነጃጅት ጋር ነው የምትወዳደረው።
"ፍልስጤም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳታፊ በምትሆንበት የቁንጅና ውድድር ተሳታፊ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል” ብላለች ናዲን በኢንስታግራም ገጿ ላይ ባጋራችው አጠር ያለ መልዕክት።
 
በአሕመድ መሐመድ