Search

ሃማስ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ሃሳብን ተቀበለ

Aug 18, 2025

ሃማስ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እና የእስረኞች ልውውጥ ላይ የቀረበለትን ሀሳብ መቀበሉ ተገለፀ።

የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሃማስ በጋዛ የተኩስ አቁም እና የእስረኞች ልውውጥን በተመለከተ ከእስራኤል ጋር ለመስማማት በአካባቢያዊ አሸማጋዮች የቀረበለትን የቅርብ ጊዜ ሀሳብ መቀበሉን የቡድኑ ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከድርድሩ ጋር ቅርበት ያላቸው አንድ የፍልስጤም ባለስልጣን በበኩላቸው ለቢቢሲ እንዳሉት፤ ተቀባይነት ባገኘው የስምምነት ሃሳብ መሰረት ለ60 ቀናት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ይደረጋል።

በዚህ ጊዜ ውስጥም በዘላቂ የተኩስ አቁም እና የእስራኤል ወታደሮች ከጋዛ መውጣትን በተመለከተ ድርድሮች ይካሄዳሉ።

አጠቃላይ የስምምነቱ አካል በሁለት ምዕራፍ የሚተገበር እቅድን የያዘ ነው።

በዚህ እቅድ መሰረት፣ ሃማስ ከእስራኤላውያን ታጋቾች በሁለት ምዕራፎች እንዲለቅ ይደረጋል።

ከእስራኤል ባለስልጣናት በኩል በጉዳዩ ላይ የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩን ቢቢሲ ዘግቧል።

በአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ የቀረበውን ሃሳብ መሰረት አድርገው ግብፅ እና ኳታር ለእስራኤል እና ለሃማስ ያቀረቡት የሰላም ስምምነት ሀሳብ በአጠቃላይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና የእስረኛ ልውውጥ እንዲካሄድ ያለመ ነበር።



#EBC #ebcdotstream #peace #deals