የኢትዮጵያ ሰላም እና ልማት ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ፅንፈኞች የጥፋት አማራጫቸው የሆነውን ትሥሥር ፈጥረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንዳሉት ቀደም ሲል በተናጠል ሀገር የማፍረስ እና ሥልጣን በኃይል የመያዝ ሕልም የነበራቸው አካላት አሁን ላይ በወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አቅማቸው በመዳከማቸው ምክንያት የተስፋ መቁረጥ ጥምረት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።
ቆሞ ቀሩ የከሰረው የህወሓት ቡድን፣ በኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው ሸኔ እና በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች ያደረጉት መቀራረብ የጋራ ራዕይ ውጤት ሳይሆን የመንግሥት የኃይል ሚዛን መጠናከር ያስከተለው ፍርሃት ነው።
ይህ ጥምረት በፖለቲካም ሆነ በማኅበራዊ መስተጋብር እርስ በርሳቸው የማይጣጣሙ እና የማይታረቁ ጽንፎችን ያቀፈ ነው።
ትናንት እርስ በርስ ሲካሰሱ የነበሩ እነዚህ አካላት ዛሬ ለመሰባሰብ መሞከራቸው የቡድኖቹን መርሕ አልባነት እና የፖለቲካ ግብዝነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
እነዚህ አካላት ምንም ዓይነት ገንቢ ሀገራዊ ዓላማ፣ ግልጽ የወደፊት ራዕይ ወይም ለሕዝብ የሚጠቅም አጀንዳ የላቸውም።
አጠቃላይ እንቅስቃሴያቸውም የሚያረጋግጠው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላም፣ ልማት እና ደኅንነት ምንም ዓይነት ደንታ እንደሌላቸው እና የቆሙትም ለግል እና ለቡድን ሥልጣን ጥም ብቻ ነው።
በሀገር ውስጥ አቅማቸው እየተዳከመ በመምጣቱ እነዚህ የጥፋት ኃይሎች፣ ሀገራዊ ለውጡን ለማሰናከል እና ትርምስ ለመፍጠር ሲሉ የውጭ ኃይሎችን በር ማንኳኳት እና ድጋፍ መፈለግ ይዘዋል።
ይህ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ትሥሥር ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት፣ ሀገራዊ ችግሮችን ወደ ቀጠናዊ ውጥረት በመቀየር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ ለመጣል የተወጠነ አካሄድ መሆኑ ተጠቅሷል።
የውጭ ኃይሎችን የመጋበዝ አዝማሚያ ቡድኖቹ ለሀገር እና ለሕዝብ ያላቸውን ንቅዘትና የባንዳነት ደረጃ የሚያሳይ ነው።
የተቃራኒዎች እና የመርሕ አልባዎች ጊዜያዊ ኅብረት የኢትዮጵያን የጥንካሬ ጉዞ ሊያስቆም የማይችል ሲሆን መሬት ላይ ያለው እውነታም የመንግሥት የሕግ የበላይነት የማስከበር አቅም እየጠነከረ መምጣቱን ያመላክታል።
እነዚህ ፍጹም አጥፊ እና ሕዝባዊ መሠረት የሌላቸው ቡድኖች የሚያደርጉት ጥረት የራሳቸውን መክሰም የሚያፋጥን መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የሕግ የበላይነትን በማስከበር፣ የዜጎችን ደኅንነት በመጠበቅ እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን በጽናት በመመከት የሀገራችን የዴሞክራሲ እና የልማት ጉዞን ማስቀጠል የወቅቱ ዋነኛ ሀገራዊ ግዴታ መሆኑንም እንዲሁ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: