የኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዐይን ሐኪም እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ሕክምና ትምህርት ክፍል መሥራች ዶክተር ጳውሎስ ቀነዓ በ97 ዓመታቸው አርፈዋል።
በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ለረጅም ዓመታት ያገለገሉት ዶክተር ጳውሎስ፣ ከማከም አልፈው በሀገራችን የነበረውን የዐይን ሐኪሞች እጥረት ለመቅረፍ በ1972 ዓ.ም የዐይን ሕክምና የድህረ ምረቃ ትምህርት ክፍልን በማስጀመር በርካታ ባለሙያዎችን አፍርተዋል።
ጤና ሚኒስቴር ዛሬ ባጋራው መግለጫ፣ በእኚህ አንጋፋ እና ለብዙዎች አርዓያ በሚሆኑ የጤና ባለሙያ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን በመግለጽ ለቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: