Search

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 708 ኢትዮጵያውያን ተመለሱ

ማክሰኞ ነሐሴ 05, 2018 260

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 708 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 8 ዙር በረራ የተመለሱት 773 ወንዶች እና 677 ሴት እንዲሁም 76 ህፃናት ሲሆኑ፣ ከተመላሾች መካከል 163 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

‎መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ሥራ እስካሁን ከ92 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

‎ሚኒስቴሩ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ሥራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

‎በተጨማሪም መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ወደ ተለያዩ ሀገራት ሄደው የሚመለሱ የፍልሰት ተጎጂዎችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም የሚያስችሉ ተግባራትን በትብብር እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: