Search

በሔክታር ከ9 ወደ 21 ኩንታል፤ የኢትዮጵያ ቡና አዲስ የዕድገት አብዮት

ማክሰኞ ነሐሴ 05, 2018 157
በሀገራዊ የቡና ምርትና ምርታማነት ኢኒሼቲቭ አማካኝነት በሔክታር የሚገኘውን የቡና ምርት መጠን ከአሁን ቀደሙ 9 ኩንታል ወደ 21 ኩንታል ለማሳደግ ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ ገለፁ።
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ኢትዮጵያ የቡና መነሻ ብቻ ሳትሆን ቡና የሀገሪቱ የኢኮኖሚ አከርካሪ፣ የበርካታ ሚሊዮን አርሶ አደሮች የዕለት ተዕለት የሕይወት መሠረት እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ገቢዋ ዋና ምንጭ ነው ብለዋል።
በመሆኑም ይህንን ዘርፍ በምርታማነት፣ በጥራትና በዘላቂነት በማሳደግ፤ ምርቱን እሴት በመጨመር ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ በስፋት ማቅረብ የመንግሥት ዋነኛ ትኩረት መሆኑን አብራርተዋል።
ይህንኑ ግብ ለማሳካት የቀረበው አዲሱ የቡና ልማት ፓኬጅ አሰራሩን ከባህላዊ አካሄድ ወደ ዘመናዊ የምርታማነት ሥርዓት ያሸጋገረ ነው ተብሏል።
ለዚህም ስኬት የ10 ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ተቀርጾ፣ የልማት ፓኬጁን በማሻሻል ዘመናዊ የአመራረት ዘዴዎች በተግባር እንዲተርጎሙ መደረጉንም አንስተዋል።
በዚሁ መሠረት የምርታማነት ግቡን ለማሳካት ከ1 ነጥብ 15 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በቡና ልማት ሽፋን ስር ለማዋል ስራዎች መጀመራቸውን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: