Search

የመከላከያ ሠራዊት እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

ረቡዕ ነሐሴ 06, 2018 81

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የተደራጀ ዘመናዊ ሠራዊት ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በአጭር ጊዜ ፈጣን ዕድገት ማስመዝገብ የቻለ ተቋም መሆኑን አድንቀዋል።

ሉዓላዊነትን እና ብሔራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ ዘመናዊ ሠራዊት ለማደራጀት የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር  ወርቁ ጋቸና (/) በበኩላቸው፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለመከላከያ ኃይል በተለይም በአየር፣ በምድር እና በሳይበር ዘርፎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተው፤ ኢንስቲትዩቱ ሠራዊቱን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ይህ ስምምነት በሎጀስቲክስ፣ በሥልጠና፣ በሳይበር ደኅንነት፣ በሠራዊቱ ጤና አጠባበቅ፣ እንዲሁም በአየር ኃይል እና በኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር ዘርፎች በቴክኖሎጂ በመታገዝ የሠራዊቱን አቅም ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው።

ከስምምነቱም ጎን ለጎን በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራው ከፍተኛ ልዑክ የኢንስቲትዩቱን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ መጎብኘታቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: