ከታች ወደ ላይ ያነጣጠረ አካሄድ፡- ውይይቱ በ250 አባላት፣ በ30 አጠናቃሪዎች እና በ500 ተወካዮች መካከል ተደጋጋሚ እና በጥንቃቄ የተመራ የሀሳብ ልውውጥን መሰረት አድርጎ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
አካታችነትን ያረጋገጠ መድረክ፡- አራት ሺህ የሚሆኑ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች መጥተው በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ በእኩልነት መወያየታቸው በራሱ ትልቅ ስኬት ነው፡፡
ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረገ፡- የምክክር ጉባኤው የሁሉንም ብሎም በቁጥር አነስተኛ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን መብት እና ማንነት እውቅና የሰጠ እና ማዕከላዊ ሀሳቦችን ያነገበ መሆን ይኖርበታል፡፡
ከግል ወደ የጋራ ፍላጎት፡- ተሳታፊዎች የግል፣ የየቡድኖቻቸው ወይም የፓርቲዎቻቸው አጀንዳዎችን ብቻ ከማስቀደም ይልቅ ጠቅለል ያሉ እና የጋራ በሆኑ ሀሳቦች ላይ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል፡፡
የምክክር ባህል አዲስነት፡- አዲስ ልምድ በመሆኑ የሚፈጠሩ መቆጣት፣ ማኩረፍ ወይም ሽኩቻዎች የሚጠበቁ ሲሆን፤ ከመጠን ሲያልፉ ግን አፋጣኝ ስርዓት እንዲይዙ ይደረጋል፡፡
የቅሬታ አፈታት፡- የዕለት ተዕለት ቅሬታዎችን በቅርበት የሚሰማ እና መፍትሄ የሚሰጥ በሶስት ኮሚሽነሮች እና በሶስት ባለሙያዎች የሚመራ ቡድን ተቋቁሞ እየሠራ ይገኛል፡፡
የውሳኔ ሀሳብ ዝግጅት፡- ስምምነት ላይ በተደረሰባቸው አጀንዳዎች ዙሪያ፣ ከእያንዳንዱ 500 ተወካዮች ውስጥ 15 ሰዎች (በድምሩ 120 ሰዎች) ተመርጠው የውሳኔ ሀሳቦችን ካዘጋጁ በኋላ ለዋናው ጉባኤ (ለ4000 ተወካዮች) አቅርበው ተቀባይነትን ያገኛሉ፡፡
የአለመግባባት መፍቻ መንገዶች፡- በሂደቱ ውስጥ እንቅፋቶች ወይም አለመግባባቶች ቢፈጠሩ የሽማግሌዎች ስብስብ እንዲሁም 330 ያህል አባላት ያሉት የክልሎች ጉባኤ ጣልቃ ገብተው መፍትሔ ይሰጣሉ፡፡
የነገ ተስፋ፡- የሚነሱት ጥያቄዎች የመቶዎች እና የሺህ ዓመታት ረጅም ታሪክ ያላቸው ቢሆኑም፤ የውይይቱ ዋና ትኩረት ላለፈው ጊዜ ከመቆዘም ይልቅ ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን መፍጠር ነው፡፡
የሰነድ ማቆየት፡- የምክክሩ ሂደቶች በሙሉ ወደፊት ለፖሊሲ አውጪዎች እና ህገ-መንግስቱን ለሚመለከቱ ወይም ለሚከልሱ አካላት በግብአትነት እንዲያገለግሉ ታሪክ ሆነው ይሰነዳሉ፡፡
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: