Search

በታሪካዊ ውድቀት እየተደመደመ ያለው የሕገ-ወጡ ህወሓት የሤራ ጉዞ

ረቡዕ ነሐሴ 06, 2018 56

21ኛው ክፍለ ዘመን ሥልጣኔ ላይ የሚገኝ ማንኛውም የፖለቲካ ሥነ-ምህዳር የሚመራው በሕግ የበላይነት፣ በሕዝባዊ ተጠቃሚነት እና በጋራ ልማት ራዕይ ላይ ተመስርቶ ነው።

ይሁን እንጂ የቆሞ ቀሩና ሕገ-ወጡ ህወሓት የፖለቲካ ህልውና ይህንን ዘመናዊ የፖለቲካ ብስለት መከተል ያቃተው፣ ጊዜ ካለፈበት እና ፀረ-ሕዝብ ከሆነ አሮጌ አስተሳሰብ ጋር የተቆራኘ መሆኑን የታሪክ መዝገብ በግልጽ ያሳያል።

ይህ እኩይ ቡድን ኢትዮጵያ አሁን ከደረሰችበት የንቃተ ህሊና ከፍታ እና ዴሞክራሲያዊ አቅጣጫ ጋር መራመድ ባለመቻሉ ሁልጊዜም ብቸኛ አማራጭ አድርጎ ሲጠቀምበት የነበረው ደም አፍሳሽ ብጥብጥን፣ ሰይጣናዊ የድብቅ ሤራን እና አረመኔያዊ የሕገ-ወጥነት አካሄድን ነው።

የዚህ የጥፋት ቡድን የፖለቲካ ዝቅጠት በጉልህ የሚታየው በሀሳብ ደረጃ ሙሉ በሙሉ መክሰሩ እና ዘመኑን የሚመጥኑ አዳዲስ አጀንዳዎችን ማመንጨት አለመቻሉ ላይ ነው።

የዜጎችን የጋራ ዕድገት ከማቀድ ይልቅ የሕዝብን አንድነት ለመናድ እና በልዩነቶች ላይ የማይበርድ የጥፋት እሳት ለመጫር ከተጓዘበት የክፋት ርቀት ያተረፈው ሞትና ውድመትን ብቻ ነው።

ይህ የሃሳብ ድህነት እና የክፋት ጥግ ሀገርን ከፍተኛ ዋጋ ከማስከፈሉም ባለፈ ራሱ "ወክየዋለሁ" የሚለውን የትግራይን ሕዝብ ለአሰቃቂ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ዳርጎታል።

ባለበት የተቸነከረው ይህ ቡድን ሀገርን 27 ዓመታት በከፋፋይ የዘረኝነት ፖለቲካ እና በድህነት አዘቅት ውስጥ ከትቶ ሲያሰቃይ ቆይቶ፣ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ሕዝብ መሸከም ሲያቅተው እንደ ተባይ ከላዩ ላይ አራግፎ ጥሎታል።

ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግርን ከመቀበል ይልቅ የሽብር እና የኮንትሮባንድ ፖለቲካን መምረጡ ደግሞ ቡድኑ የመጨረሻው የፖለቲካ መክሰር ደረጃ ላይ የደረሰ አጥፊ ኃይል መሆኑን በግልጽ አሳይቷል።

እነዚህ የጥፋት ኃይሎች በሕዝቡ ተገፍተው ከሥልጣን ከተባረሩ በኋላም ሀገራዊ ተቋማትን ለማፍረስ እና ብሔራዊ ሉዓላዊነትን ለባዕዳን አሳልፎ ለመስጠት ያደረጉት አሳፋሪ ሙከራ ሁሉ በሕዝቡ አርቆ አሳቢነትና ፅናት ተቀብሯል።

ይህ ከፋፋይ የፖለቲካ አስተሳሰብ በታሪክ ሂደት ውስጥ ወደ ዳር ተገፍቶ እየተሸነፈ መምጣቱ የኢትዮጵያን የውስጥ አንድነት እና የሕዝቧን የፅናት ልክ ይበልጥ ያሳየ ክስተት ሆኗል።

የቡድኑ የሤራ ፖለቲካ ጊዜያዊ እክሎችን ሊፈጥር ቢችልም የነቃ እና ሰላሙን የሚጠብቅ ማኅበረሰብን ፍላጎት ማሸነፍ እንደማይችል አሁን ሕገ-ወጡ ህወሓት የሚገኝበት የሞት ጣር ግልጽ ማረጋገጫ ነው።

ይህ የፖለቲካ ዝቃጭ ፍጻሜውን ማግኘቱ ዕውን እየሆነ ነው፡፡ ኢትዮጵያም ካረጁ የፖለቲካ ማነቆዎች ሙሉ በሙሉ ተላቅቃ ወደ ላቀ ምዕራፍ የምትሸጋገርበት ጎዳና ላይ ትገኛለች።

አሁን ላይ ሀገራችን የጀመረችው ሀገራዊ የምክክር መድረክ፣ የሽግግር ፍትህ ሥርዓት ትግበራ፣ እንዲሁም ሕጋዊነትን የማክበር እና ተቋማዊ አቅምን የመገንባት ጉዞ የትኛውም የከሰረ አሮጌ አስተሳሰብ ሊያስቆመው የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

የህወሓት አፍራሽ እና እኩይ ሤራዎች በሕዝብ ፅናት ፊት ሙሉ በሙሉ ተሸናፊ መሆናቸው፡፡ የሤራ ፖለቲካ ዝቅጠት መጨረሻው ታሪካዊ ውድቀትና ኪሳራ ብቻ መሆኑን ያረጋገጠ የመጨረሻ ፍርድ ነው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: