ኢንግላንድ ውስጥ "ሲምሰን ሞቢሊት" በተሰኘ ፋብሪካ የአንድ ቤተሰብ 5 ትውልዶች ተቀጥረው መሥራታቸው ተሰምቷል።
የቤተሰቡ 3ኛ ትውልድ የሆኑት የ91 ዓመቷ ሚጊ ኦርሌጅ በድርጅቱ ውስጥ እ.አ.አ በ1965 እና 1994 መካከል የአባታቸውን እና የአያታቸውን ፈለግ በመከተል ሠርተዋል።
ከሚጊ፣ ከአባታቸው እና ከአያታቸው ባሻገርም በዚህ ድርጅት ልጃቸው እና የልጅ ልጃቸው ተቀጥረው ሰርተዋል።
5 ትውልዶችን ያስተናገደው ይህ ድርጅት ታዲያ ልዩ ታሪክ ባለው ቤተሰብ ዘንድ ተወዳጅ መሆኑም ይነገራል።
የ91 ዓመት አዛውንት የሆኑት ሚጊ ኦርሌጅ ከድርጅቱ የቀድሞ ሰራተኛ ልጃቸው ኬቨን እና በአሁን ሰዓት በሥራ ላይ ከሚገኘው የልጅ ልጃቸው አሌክስ ጋር በመሆን ድርጅቱን በቅርቡ ጎብኝተዋል።
ለሚጊ፣ ጉብኝቱ በትውስታዎች የተሞላ ነበር። በጉብኝታቸው ወቅት የቀድሞ ባልደረቦቻቸውንም ማግኘታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ከጉብኝታቸው በኋላ ታዲያ ሚጊ ይህ ቦታ ለቤተሰባቸው በአምስት ትውልዶች ውስጥ ያለፈ የትዝታ እና የኩራት ስፍራ መሆኑን በማንሳት በስፍራው በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
በሴራን ታደሰ
#EBC #ebcdotstream #work