Search

አንጋፋ የታሪክ ተመራማሪ እና የሀገር ሽማግሌ የነበሩት የአቶ አብርሃም ባቾሬ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ

እሑድ ነሐሴ 10, 2018 82

የወላይታ ሕዝብ ታሪክ ተመራማሪ እና የሀገር ሽማግሌ የነበሩት የአቶ አብርሃም ባቾሬ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት ተፈፅሟል።

በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የወላይታ ዞን እና የሶዶ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሥራ ባልደረቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል።

የፖለቲካል ሳይንስ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር የነበሩት አቶ አብርሃም ባቾሬ፣ ትውልድን በማነጽ፣ በአስተዳደር ሥርዓት ግንባታ እና ማኅበራዊ ትሥሥርን በማጠናከር ረገድ ታላቅ ሚና የተወጡ ነበሩ።

የሦስት ልጆች አባት የነበሩት አቶ አብርሃም፣ ባደረባቸው የጤና እክል ምክንያት የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: