በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በዲላ ከተማ ባለፈው በጀት ዓመት ታቅደው በመንግሥት እና በሕዝብ ተሳትፎ የተከናወኑ ልዩ ልዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት በቅተዋል።
ከ570 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው እነዚህ ፕሮጀክቶች፣ የነዋሪዎችን ሁለገብ የልማት ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ናቸው።
ከተመረቁት ፕሮጀክቶች መካከል የዲላ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ለኢንተርፕራይዞች የተዘጋጁ የማምረቻና መሸጫ ሼዶች፣ የማሞ ኮሞልቻ የሕዝብ መዝናኛ ማዕከል እንዲሁም በኮሪደር ልማት የተገነቡ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች ይጠቀሳሉ።
በተጨማሪም "ሰባ ቤቶች በሰባ ቀናት" በሚል መሪ ቃል ለአቅመ ደካሞች እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች በአጭር ጊዜ የተገነቡ 70 ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶችም የምረቃው አካል ነበሩ።
ከቤቶቹ መካከል 20 ያህሉ ባለ ሁለት መኝታ ሲሆኑ፣ የተቀሩት ባለ አንድ መኝታ ናቸው።
በትዕግስቱ ቡቼ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: