በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ወጣቶች እና ታዳጊዎች ለአዲሱ የትምህርት ዘመን በሥነ ልቦና፣ በቁሳቁስ እና በሞራል ከፍተኛ ዝግጅት የሚያደርጉበት ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ እና ነጋቸውን በዕውቀት ለመገንባት የሚያልሙበት ልዩ ወቅት ላይ ይገኛሉ።
በየክልሉ የሚገኙ ተማሪዎች ደብተሮቻቸውን እና የመማሪያ ቁሳቁሶቻቸውን አዘጋጅተው አዲስ የዕውቀት ምዕራፍ ለመጀመር በጉጉት የሚጠበቁበት ጊዜም ነው።
ነገር ግን ይህ ደስታ እና የትምህርት ጅማሮ ለትግራይ ወጣቶች እና ታዳጊዎች እውን ሊሆን አልቻለም።
የክልሉ ወጣቶች ከትምህርት ገበታ፣ ከሰላማዊ ሕይወት እና ከብሩህ ተስፋ ይልቅ በሞት እና በሕይወት መካከል በሚወዛወዝ አሰቃቂ እና መሪር እውነታ ውስጥ ይገኛሉ።
የከሰረው የህወሓት ቡድን ክልሉን ብቻ ሳይሆን የወጣቶችን እና የታዳጊዎችን የነገ ተስፋ በግልጽ እያደናቀፈ ነው።
የቡድኑ አምባገነናዊ እና ግትር አካሄድ ክልሉን ወደአልተቋጨ ቀውስ እና ምስቅልቅል ከመምራቱም በላይ የአዲሱን ትውልድ ሕይወት እና ጊዜ በከንቱ እያባከነ ይገኛል።
ወጣቶች ዕውቀት፣ ክህሎት እና የሥነ ልቦና ዝግጁነት የሚያገኙበት ወሳኝ የዕድሜ ክልል ላይ እያሉ በፖለቲካዊ ሴራ እና ግጭት ምክንያት ሕልማቸው አደጋ ተጋርጦበታል።
የትግራይ ታዳጊዎች የትምህርት ቤት ደወል ከመስማት ይልቅ የጦርነት ነጋሪት እየተጎሰመባቸው የከፋ የሥነ ልቦና ጫና እና የተስፋ መቁረጥ አደጋ ተደቅኖባቸዋል።
ይህ ደግሞ በነገው ትውልድ ሥነ ልቦና ላይ የሚተው ጠባሳ በቀላሉ የሚጠገን አይደለም።
ሕገ ወጡ ህወሓት የሀገር ተስፋ የሆኑትን ታዳጊዎች እና ወጣቶች ከትምህርት፣ ከዕድገት እና ከዘመናዊ ዕውቀት የማራቅ እኩይ ተግባሩን እየገፋበት ነው።
ይህ የከሰረው ቡድን የክልሉን ሥልጣን እና የገዛ ፖለቲካዊ ሕልውናውን ብቻ ለማስቀጠል በሚያደርገው እኩይ እና ኃላፊነት የጎደለው እንቅስቃሴ የትግራይን አዲሱን ትውልድ ለባሰ ጨለማ እና ለድህነት አሳልፎ እየሰጠ ይገኛል።
ወጣቶች እና ታዳጊዎች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምርምር እና በዕውቀት መበልጸግ በሚገባቸው ወሳኝ ወቅት የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው እንዲጨልም መደረጉ የክልሉን የወደፊት ዕድገት ብቻ ሳይሆን የሀገርንም የነገ ተስፋ የሚጎዳ ታሪካዊ ስህተት ነው።
የትግራይ ወጣቶች እና ታዳጊዎች ከፖለቲካዊ ቁማር እና ለሥልጣን ከሚደረግ እልህ ይልቅ ሰላም፣ ትምህርት፣ ሥነ ልቦናዊ እፎይታ እና ብሩህ አድማስ ያስፈልጋቸዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: