Search

ሀገራዊ ምክክር መተማመንን የሚፈጥር እና ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች ሀገር የሚያስረክብ ነው፦ ተመካካሪዎች

እሑድ ነሐሴ 10, 2018 63

ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ መተማመን እና አንድነትን ለመገንባት የሚያደርገው ሀገራዊ የምክክር ሒደት በስኬት እየተከናወነ ይገኛል።

ይህ ታሪካዊ የምክክር መድረክ ለዘመናት ምላሽ ያጡ ጥያቄዎችን በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት የዜጎችን እኩል ተሳትፎ በማረጋገጥ ለነገዋ ኢትዮጵያ ፅኑ መሠረት በመጣል ላይ ነው።

በምክክር መድረኩ ላይ የተሳተፉ ተመካካሪዎች እንደገለጹት ኮሚሽኑ ያዘጋጀው መድረክ ከዚህ ቀደም ድምፃቸው የማይሰማ እና አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን ብሔረሰቦች ያካተተ በመሆኑ አካታችነቱን በተግባር አሳይቷል።

የምክክሩ ሒደት ከጥቃቅን ቡድኖች በመነሳት በሒደት ወደ 500 ተሳታፊዎች ያደገበት አሠራር መሆኑን የጠቀሱት ተመካካሪዎቹ፣ ይህም በየደረጃው ሰፊ ውይይት ለማድረግ እና በጋራ አጀንዳዎች ላይ መግባባት ላይ ለመድረስ ማስቻሉን ገልጸዋል።

ይኸው አሠራር በዜጎች መካከል ለዓመታት የነበሩ የተደራረቡ አለመተማመኖችን ለማስወገድ ግልጽ ውይይት ለማድረግ እና እርስ በርስ የመከባበር ባሕልን ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በተጨማሪም ውይይቱ ያለምንም ጫና፣ እያንዳንዱ ተሳታፊ በራሱ ቋንቋ እና ፍላጎት አጀንዳዎቹን ያቀረበበት መሆኑን በመጥቀስ እስካሁን በጽንሰ ሐሳብ ደረጃ የነበረውን የዴሞክራሲ ልምድ በተግባር ለመለማመድ መድረኩ ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን ተናግረዋል።

ተመካካሪዎቹ አጀንዳዎቹ በሙሉ በቃለ ጉባኤ ተይዘው ለሚመለከታቸው አካላት የሚተላለፉ በመሆናቸው ውጤታማ መፍትሔ እንደሚገኝበት እምነታቸውን ገልጸዋል።

የመደማመጥ እና ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል ተቋማዊ ሆኖ መቀጠል እንዳለበት ተመካካሪዎቹ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሒደቱ በየዓመቱየሀገራዊ ምክክር ሳምንትአልያምቀንእየተባለ የሚዘከር ባሕል ቢሆን ለቀጣዩ ትውልድ በፍቅር፣ በአንድነት እና በውሕደት የተገነባች የተሻለች ሀገርን ለማስረከብ ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሆን አስገንዝበዋል።

በሃና ምንዳሁን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: