Search

የመደመር እሳቤን በተግባር ያረጋገጠው የሐረሪ ክልል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንቅስቃሴ

ሓሙስ ነሐሴ 14, 2018 97

"መደመር" እሳቤ የትብብር፣ የመተማመን፣ የአንድነት እና የጋራ ኃላፊነት መርህን በማጠናከር የሀገር ግንባታን ለማፋጠን የሚያበረታታ ነው።

መደመር የልዩነትን ኃይል ወደ ጋራ ጥቅም የሚቀይር እሳቤ እንደሆነው ሁሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም ይህንን ፍልስፍና በተግባር ያንጸባርቃል።

ዜጎች ዕውቀታቸውን፣ ጊዜያቸውን እና ጉልበታቸውን በማዋሃድ የማኅበረሰብን ችግሮች በጋራ ሲፈቱ የአንድነት መንፈስ ይጠናከራል፤ የመተማመን ባህልም ይጎለብታል።

በመደመር ዘመን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከግለሰብ ተሳትፎ ባለፈ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በመሆን በሐረሪ ክልል የመደመርን ፍልስፍና በሚያያንፀባርቅ መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

በዚህም በክልሉ ባለፉት ዓመታት በሰው ተኮር ሥራዎች እና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።

ለአብነትም ባለፉት አምስት ዓመታት በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብሮች የአቅመ ደካሞችን ቤት የመገንባት እና የማደስ፣ የትምህርት ቤቶችንና የጤና ተቋማትን የማደስ ሥራዎች ተከናውነዋል።

በተጨማሪም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች ከመተከላቸውም ባሻገር የነፃ ሕክምና፣ የአካባቢ ጽዳት እና የቆሻሻ ማስወገድ ሥራዎች በበጎ ፈቃደኞች ተከናውነዋል።

ለአረጋውያን እና ለአካል ጉዳተኞች ማዕድ ማጋራት፣ የአልባሳት እና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ እንዲሁም የደም ልገሳ ተግባራት በሰፊው ተካሂደዋል።

ለተማሪዎች እና ለትምህርት ቤቶች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ፣ የትምህርት ቤት ግንባታና እድሳት እንዲሁም የቤተ መጻሕፍት ማደራጀት ሥራዎችም በበጎ ፈቃደኞች ተከውነዋል።

ይህ የበጎ ፈቃድ ባህል በያዝነው የክረምት ወራት 14 የተለያዩ ዘርፎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ ለዘላቂ ልማት፣ ለማኅበራዊ አንድነትና ለሀገራዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: