Search

በመከላከያ እና ደኅንነት ዘርፍ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ ትብብር ለመመስረት ተስማሙ

ዓርብ ነሐሴ 15, 2018 103

በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር ጄኔራል በሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ነሐሴ 13 እና 14 ቀን 2018 . በአሜሪካ ያደረገውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ተከትሎ በፔንታጎን ከአሜሪካ የመከላከያ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ፍሬያማ ውይይት አካሂዷል።

ከአሜሪካው የአፍሪካ ጉዳዮች የመከላከያ ምልከታ ምክትል ረዳት ጸሐፊ ብሪያን . ኤሊስ ጋር በጋራ በተመራው በዚህ ምክክር፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረውን ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ወደ ላቀና አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር ሙሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

የሁለቱ ሀገራት የመከላከያ ተቋማት አመራሮች ተቋማዊ ትብብራቸውን ለማስፋፋትና ስትራቴጂካዊ ቅንጅታቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል።

ይህ ሁለንተናዊ አጋርነት ሀገራዊ ጥቅምንና የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ፣ የእርስ በእርስ እምነትን በማጠናከር ዘላቂ ትብብር በሚፈጥሩ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድና በአካባቢው ዘላቂ ሰላም፣ ደኅንነትና መረጋጋትን በሚያረጋግጡ ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ ተመስርቶ የሚመራ ይሆናል።

ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ እና ምክትል ረዳት ጸሐፊ ብሪያን . ኤሊስ የተደረሱ ስምምነቶችን በፍጥነት ወደ ተግባር በመቀየር የሁለትዮሽ የመከላከያ ግንኙነቱን ወደ ተሻለና ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሳደግ ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ልዑኩ በቆይታው ከሌሎች የአሜሪካ መከላከያ ተቋማት አመራሮች ጋርም ሰፊ ውይይቶችንና ጉብኝቶችን አድርጓል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: