አንጋፋው አርቲስት ደበበ እሸቱ በሙያው ስሙን የተከለ አንጋፋ የመድረክ ሰው ነው ፟ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሸንካ ተናገሩ።
ሚኒስትሯ አክለውም አርቲስት ደበበ እሸቱ ከራስ ጥቅም በላይ ለአገር ሰርቶ ያለፈ አርአያ የሚሆን ነው ብለዋል ።
አርቲስት ደበበ ከኢትዮጵያ አልፎ በሆሊውድ የፊልም ኢንዱስትሪ አሻራውን ያሳረፈ መሆኑንም ተናግረዋል ።
ከራስ ጥቅም በላይ ለአገር ጥቅም መስራትን በተግባር ያሳየ የጥበብ አርበኛ መሆኑንም ነው ሚኒስትሯ የገለጹት።
አርቲስት ደበበ በእውቀቱ እና በልምዱ ብዙ ማገልገሉን ገልጸው ለመላው ቤተሰብ እና ለሙያ አገሮቹ መጽናናትን ተመኝተዋል።
በሽኝቱ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ፣የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ ፤ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ፣የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካን ጨምሮ ሚኒስትሮችና የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በዘአማኑኤል መንግስቱ