የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለው ከባድ ሰደድ እሳት በስፔን እና በፖርቱጋል ደኖችን እና መንደሮችን በከፍተኛ ሁኔታ እያወደመ ይገኛል።
ሁለተኛ ሳምንቱን የያዘው ሰደድ እሳቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓል።
በስፔን እና በፈረንሳይ በድምሩ 2 የእሳት አደጋ ሰራተኞች መሞታቸውን ተከትሎም የሃገራቱ ሟች ቁጥር ወደ 6 ከፍ ብሏል።
እንደ አልጀዚራ ዘገባ እስካሁን በዚህ አመት በመላ ፖርቹጋል ወደ 216 ሺህ ሄክታር መሬት ወድሟል።
እንዲሁም ከ343 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስፔን የወደመ ሲሆን ከሶስት አመት በፊት ከተመዘገበው 36ሺ ሄክታር መሬት ይበልጣል።
የአውሮፓ የደን እሳት መረጃ ስርዓት እንዳሳወቀው የስፔን ሰደድ እሳት አዲስ ብሔራዊ ሪከርድን አስመዝግቧል።
ሰደድ እሳቱ ከፍተኛ የሙቀት መጠንን በማስመዝገብ ላይ ሲሆን፤ የአየር ለውጥ ሁኔታዎች ቀውሱን ሊያራዝሙ እንደሚችሉ ባለስልጣኖች አስጠንቅቀዋል።
በሴራን ታደሰ
#ebc #ebcdotstream #Spain #Portugal #wildfires