Search

የአርቲስት ደበበ እሸቱ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

ማክሰኞ ነሐሴ 13, 2017 122

የአርቲስት ደበበ እሸቱ ስርዓተ ቀብር 4 ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

በቀብር ስነ-ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የአርቲስት ደበበ እሸቱ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች እና አድናቂዎች ተገኝተዋል፡፡

የአርቲስት ደበብ እሸቱ የአስከሬን ሽኝት መርሐ ግብር በብሔራዊ ቴአትር የተከናወነ ሲሆን፤ በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይም የአርቲስት ደበበ እሸቱ ሥራዎችን የሚያሳይ ዶክመንተሪ ቀርቧል፡፡

ከሽኝት መርሐ ግብሩ በኋላም የአርቲስት ደበበ እሸቱ የቀብር ስነ-ስርዓት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

አርቲስት ደበበ እሸቱ በኢትዮጵያ ዘመናዊ የኪነ ጥበብ ታሪክ ታላቅ ዐሻራ ያኖረ አርቲስት እንደነበር በህይወት ታሪኩ ላይ ተገልጿል።

በዘአማኑኤል መንግስቱ

#ebcdotstream #EBC #DebebeEshetu