Search

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ከታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ዓርብ ነሐሴ 22, 2018 64

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሀሳክ ፉዋንግኬትኬዎን በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ።

በውይይታቸው ወቅት በኢትዮጵያ እና በታይላንድ መካከል ስላለው የረጅም ጊዜ ግንኙነት ሰፊ ምክክር ማድረጋቸውን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል።

የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት እና የትብብር መስኮችን ይበልጥ ማጠናከር እና ማሳደግ በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያም ሐሳብ መለዋወጣቸው ተገልጿል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: