በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 76ኛው የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ጉባኤ (RC76) ተሳታፊ ልዑካን በአዲስ አበባ የሚገኙ የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎችን ጨምሮ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎብኝተዋል።
ተሳታፊዎቹ ከየአባል የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የጤና ሚኒስትሮች እና የዓለም የጤና ድርጅት አከፍተኛ መራሮች፣ ከተለያዩ የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲዎች የመጡ ተወካዮች፣ የልማት አጋሮች እና በርካታ ዓለም አቀፍ ታዳሚዎች ናቸው።
ጉብኝቱ እንግዶቹ አህጉራዊ የጤና አጀንዳዎችን ከመምከር ባለፈ፣ ከተማችን በቱሪዝምና በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ እያስመዘገበች ያለውን ፈጣን ለውጥ በቅርበት እንዲያዩ ልዩ አጋጣሚ ፈጥሮላቸዋል።
በርካታ ሀገራት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማትን ያሰባሰበው ይህ ጉባኤ፣ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ መድረኮችን በብቃት የማስተናገድ አቅሟን ከማረጋገጡም በላይ፣ የቱሪዝም ፀጋዎቿን እና የልማት ሥራዎቿን ለዓለም ለማስተዋወቅ ትልቅ ፋይዳ አለው።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: