Search

የሰው ልጅን ተፈጥሯዊ ክብር ማዕከል ያደረገ በጎ ተግባር፡ ከሥራ ፈጠራ እስከ ኅብረተሰብ ጤና

ዓርብ ነሐሴ 22, 2018 122

በከተማችን አዲስ አበባ የተጀመረው መልካም አስተዳደርን የማስፈን እና የዕድገት ጉዞ የዜጎችን ሕይወት በቀጥታ በመቀየር ረገድ ትልቅ ስኬት እያመዘገበ ይገኛል።

በተለይ በከንቲባ አዳነች አቤቤ አነሳሽነት በከተማዋ ተገንብተው ሥራ የጀመሩት ዘመናዊ የእንጀራ ፋብሪካዎች የአስተዳደሩ የሰው ተኮር ፖሊሲ ቁልፍ ማሳያ ሆነው ብቅ ብለዋል።

እነዚህ ማዕከላት ለበርካታ እናቶች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የቤት ውስጥ ጫናቸውንና የኢኮኖሚ ጥገኛነታቸውን በመቅረፍ በራሳቸው እግር እንዲቆሙ ያደረጉ እውነተኛ የእናትነት አለኝታዎች ሆነዋል።

ፋብሪካዎቹ ከዚህ ቀደም በአንዳንድ አካላት ይፈጸም የነበረውንና የሕዝብን ጤና አደጋ ላይ ይጥል የነበረውን እንጀራን ከባዕድ ነገሮች ጋር ቀላቅሎ የማዘጋጀት እኩይ ተግባር  እንዲቆም አድርገዋል።

በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዙት እነዚህ ማዕከላት ጥራቱ የተጠበቀና ጤናማነቱ የተረጋገጠ ምርት ለሕብረተሰቡ በማቅረብ የነዋሪዎችን የጤና ደህንነት አስተማማኝ ባደረገ መልኩ እያገለገሉ ይገኛሉ።

የዚህ በጎ ተግባር ሌላኛው ገጽታ ምርቱን ተረክበው ለኅብረተሰቡ የሚያቀርቡ አከፋፋዮችን ቀጥተኛ ተጠቃሚ ማድረጉ ነው።

ሕጋዊና አስተማማኝ የምርት አቅርቦት በመፍጠሩ፣ አከፋፋዮቹ ጥራቱ የተረጋገጠ ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ በማግኘት ሥራቸውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲያካሂዱና ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ ትልቅ ዕድል ፈጥሮላቸዋል።

ይህ በጎ ተግባር እናቶችን ከማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ከመገላገሉም በላይ፣ የህዝብን ጤና በመጠበቅ እና ለአነስተኛ ነጋዴዎች የሥራ ዕድል በመክፈት ሰው ተኮር ልማት ለነዋሪዎች ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ አጉልቶ ያሳያል።

በሔዋን ጌታቸው

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: