Search

ቼልሲ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ

እሑድ ነሐሴ 24, 2018 292

በ2ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስታምፎርድ ብሪጅ ላይ ብራይተንን ያስተናገደው ቼልሲ 4 ለ 3 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ሮሚዮ ላቪያ ለቼልሲ የመጀመሪያውን ግብ ባስቆጠረበት ጨዋታ፣ ፔድሮ ኔቶ እና ጆዋዎ ፔድሮ ተጨማሪ ግብ አስቆጥረው ቼልሲ 3 ለ 0 እንዲመራ አስችለው ነበር።

ሆኖም ማሊክ ጁኒየር ለብራይተን አስቆጥሮ የመጀመሪያው አጋማሽ በቼልሲ 3 ለ 1 መሪነት ተጠናቅቋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ጆዋዎ ፔድሮ በራሱ መረብ ላይ ያስቆጠራት ግብ ውጤቱን ወደ 3 ለ 2 ብታጠብም፣ ኮል ፓልመር ተጨማሪ ግብ አስቆጥሮ ቼልሲን 4 ለ 2 መሪ አድርጓል። በጭማሪ ሰዓት ፓስካል ግሮስ ያስቆጠራት ግብ ብራይተንን ከሽንፈት አልታደገችም።

ጨዋታው 4 ለ 3 በሆነ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ቼልሲ በሁለት ተከታታይ ደሎቹ ነጥቡን ስድስት ሲያደርስ፣ በሁለቱ ጨዋታዎች በተጋጣሚዎቹ መረብ ላይ ያስቆጠራቸው ግቦች 7 ሆነዋል።

ቼልሲ በ3ኛው ሳምንት የሊጉ መርሐ-ግብር በቀጣይ ሳምንት እሁድ ሻምፒዮኑን አርሰናል በኢሚሬትስ ይገጥማል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: