ማንቸስተር ዩናይትድ አዲሱን የውድድር ዓመት በሽንፈት ይጀምር እንጂ፣ ካለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ በኋላ ቡድኑን በተረከበው ማይክል ካሪክ ስር ያሳየው ለውጥ በአዲሱ የውድድር ዓመት ብዙ እንዲጠበቅበት ያደረገ ሆኗል።
ከአንጋፋው አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ስንብት በኋላ ለአስራ ሦስት ዓመታት ወደራቀበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነት መመለስ፣ ብሎም በአውሮፓ መድረክ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን በአዲሱ የውድድር ዓመት የማንቸስተር ዩናይትድ ውጥኖች ናቸው።
ዩናይትድ በዝውውር መስኮቱ በአመዛኙ የመሀል ክፍሉን በማጠናከሩ ላይ ነው ትኩረት ያደረገው። አንድሬ ሳንቶስ ከቼልሲ፣ ዮሪ ቴሌማንስ ከአስቶንቪላ እንዲሁም ካርሎስ ባሌባ ከብራይተን፤ በማንቸስተር ዩናይትድ የዝውውር እንቅስቃሴ ወስጥ ጉልህ ስፍራ የሚሰጣቸው ዝውውሮች ሆነዋል።
በአንፃሩ ካሰሚሮን ጨምሮ በርካታ ተጫዋቾቻቸውን በውሰትና በቋሚ ዝውውር አሳልፈው ሰጥተዋል። የማንቸስተር ዩናይትድን የቅርብ ዓመታት ውጤት አልባ መንገድ መቀየርና የቀደመ ታሪኩን የሚመጥን የስኬት ጎዳና ላይ መገኘት የማይክል ካሪክ ስብስብ እቅድ ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ በ2ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ነገ ምሽት 12፡30 ሰዓት በኦልድትራፎርድ ኢፕስዊች ታውንን ያስተናግዳል።
የማንቸስተር ዩናይትድ የዝውውር ተሳትፎ የፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንነትን ጨምሮ ቡድኑን አጠናክሮ ወደ ውጤታማነት ይመራዋል ብላችሁ ታስባላችሁ? ሃሳባችሁን አጋሩን።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: