Search

ብሩኖ ፈርናንዴዝ ሃትሪክ በሰራበት ጨዋታ ማንቸስተር ዩናይትድ ኢፕስዊች ታውንን 5 ለ 2 አሸነፈ

እሑድ ነሐሴ 24, 2018 111

2026/ 27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት የውድድር ዓመቱን ወደ ሊጉ አዲስ አዳጊ በሆነው ሀል ሲቲ ተሸንፎ የጀመረው ማንቸስተር ዩናይትድ፣ በኦልድትራፎርድ ሌላኛውን አዲስ አዳጊ ኢፕስዊች ታውንን አስተናግዶ 5 2 አሸንፎ በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ድሉን አስመዝግቧል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ሌይፍ ዴቪስ ባስቆጠራት ግብ ኢፕስዊች ታውን መምራት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም፣ ከቀናት በፊት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋችነት ሽልማትን የተቀበለው ብሩኖ ፈርናንዴዝ በጨዋታና በፍፁም ቅጣት ምት(3) ጃኮብ ገሪቭስ በራሱ መረብ ላይ እንዲሁም ብሪያን እምቡሞ ያስቀጠሯቸው ግቦች ማንቸስተር ዩናይትድን አሸናፊ አድርገዋል።

በጨዋታው ፍፃሜ ላይ ቹማ አፕኮም ያስቆጠራት ግብ ኢፕስዊችን ከሽንፈት አልታደገችም።

ከብራይተን ክለቡን አዲስ የተቀላቀለውና ጉዳት ላይ የሚገኘው ካሜሩናዊው ካርሎስ ባሌባ በኦልድትራፎርድ ከደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: