Search

“የሕወሓት እውነተኛ ገጽታ ክህደት እና ሕዝብን መበዝበዝ ነው”፦ ዶክተር ሺሻይ አማረ

ማክሰኞ ነሐሴ 26, 2018 110

 ኋላ ቀሩ የሕወሓት ቡድን እውነተኛ ገጽታ ክህደት፣ ብዝበዛ እና አምባገነንነት ነውሲሉ የሥምረት ፓርቲ ምክር ቤት አባል ዶክተር ሺሻይ አማረ ተናገሩ።

ዶክተር ሺሻይ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት በቅርቡ በሚወጡ መግለጫዎች እና ክስተቶች እንደታየው፣ በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሰው ሕገ ወጡ የሕወሓት ቡድን የሚያደርጋቸው የክህደት እና የባንዳነት ተግባራት ቁልጭ ብለው እየወጡ ይገኛሉ።

የዚህ ስብስብ ታሪካዊ እና አሁናዊ አካሄድ ዋነኛ ዓላማው የሕዝብን ጥቅም ማስጠበቅ ሳይሆን የጥቂት አካላትን ሥልጣን እና የግል ፍላጎት ማስቀጠል እንደሆነም አንስተዋል።

የቡድኑ የገንዘብ እና የበጀት ምንጭ የሕዝቡን የጋራ ሀብት እና መሬት በግልጽ ለመዝረፍ ከተዘረጋ አሠራር ጋር የተያያዘ ስለመሆኑም ነው የጠቆሙት።

የትግራይ መሬት እና የማዕድን ሀብት በግፍ ተነጥቆ ለሻዕቢያ እና ለሱዳን አካላት ከሚሸጥበት፣ ወጣቶችን ለተለያዩ አካላት አሳልፎ በመስጠት በዶላር ከሚደረግ ንግድ የሚገኝ ገቢ የቡድኑ ዋና የፋይናንስ ምንጭ ነው፤ ይህ ዓይነቱ ብዝበዛ ደግሞ የክልሉን የወደፊት ተስፋ እና ወጣቶች ለአደጋ የሚያጋልጥ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል፣ ቡድኑ ለሥልጣኑ እና ለጥቅሙ ስጋት ናቸው ብሎ የሚያስባቸውን ማናቸውንም አካላት የማስወገድ ጽንፈኛ ባሕርይ አለው።

ሥልጣኑ ከተነካ የትግራይን ሕዝብ ይቅርና የቅርብ ዘመዶቹን እንኳ የማይምር፣ ማንኛውንም ዓይነት የሐሳብ እና የፖለቲካ ልዩነት በጭራሽ የማያስተናግድ አምባገነናዊ መዋቅር ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ይህንን ጨካኝ እና የቆየ ባሕርይውን በግልጽ የሚያሳየው፣ የስብሐት ነጋ ታሪካዊ ምሥክርነት እንደሆነም ዶክተር ሺሻይ አስታውሰዋል።

ስብሐት በሰጠው መግለጫ "ዮሐንስ የሚባል ጓደኛዬ የሚመራው ግገሓት የሚባል ድርጅት በሐሳብ ከእኛ ጋር ስላልነበረ ደምስሰናቸዋል" ሲል ተናግሮ ነበር፤ ይህ አባባል ቡድኑ ገና ከመነሻው ጀምሮ የተለየ ሐሳብን በኃይል ከማጥፋት፣ ወዳጅነት እና የትግል ጓደኝነትን ለሥልጣን ሲል መሥዋዕት ከማድረግ ወደኋላ የማይል በግፍ የታነጸ አምባገነን መሆኑን ያረጋግጣል ብለዋል።

በጎሳዬ /ኪዳን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: