Search

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋራ

ሰኞ ጳጉሜን 02, 2018 135

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2019 አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ "አዲሱን ዓመት በአገልጋይነት እና በበጎነት" በሚል መሪ ቃል ለአቅመ ደካማ ወገኖች ማዕድ አጋርቷል።

በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ በተካሄደው የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ዲስትሪክት ዳይሬክተር ሲሳይ ደጀኔ ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እና የሕዝብ አጋርነቱን ለመግለጽ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በመመደብ የማዕድ ማጋራት መርሐ-ግብር ያከናውናል ብለዋል።

2019 አዲስ ዓመትን በማስመልከት በቃሊቲ ዲስትሪክት 200 አቅመ ደካማ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን ሲሳይ ጨምረው ገልጸዋል።

የኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ ምክትል አስተዳዳሪ ኬምቦን ሞቱማ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቅመ ደካማ ወገኖችን ለመደገፍ በራሱ ተነሳሽነት መልካም ሥራ በማከናወኑ አመስግነው፤ ባንኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ወገኖቹን መደገፉ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ባንኩ 2019 አዲስ ዓመትን በማስመልከት በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ አቅመ ደካማ ወገኖችን ለመደገፍ 72 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡን ታውቋል።

ድጋፉን ያገኙ አቅመ ደካማ ወገኖችም፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ችግራቸውን በመገንዘብ ከጎናቸው በመቆሙ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በብሩክታዊት አስራት

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: